01
Jul
መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል። የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ የተገኘው ትርፍ ባንኩ ባለፉት ጊዜያት ካጋጥሙት የህልውና አደጋ መውጣቱን ያሳያል ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ባንኩ ከስድስት ዓመታት በፊት ከነበረበት ችግር ወጥቶ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ ከሚባሉ ጠንካራ ባንኮች ተርታ መሰለፉንም ተናግረዋል። ባንኩ ለደረሰበት ከፍተኛ የትርፍ መጠን በዋናነት ለግል ዘርፉ የሰጠው ትኩረት፣ የተበላሸ ብድር መጠን መቀነሱ እና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት መስፋፋትን በምክንያትነት አንስተዋል። ባንኩ እየተጠናቀቀ ባለው የዘንድሮው በጀት ዓመት 648 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድር እንደሰጠም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል። ከተሰጠው ብድር ውስጥም 90 በመቶ የሚሆነውን ወይም 588 ቢሊዮን ብር ለግል ዘርፍ መቅረቡም ተገልጿል።…