18
Mar
ንግድ ባንክ ባሳለፍነዉ አርብ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ባጋጠመዉ ችግር 25 ሺ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መደረጉና 2.6 ቢሊየን ብር መንቀሳቀሱን አስታውቋል ባንኩ ገንዘብ የወሰዱ ሰዎችን ለመጠየቅና ገንዘቡን ለማስመለስ ግብረሀይል ያቋቋመ ሲሆን በባንኩ ዲጂታል መዋቅር ላይ በውስጥ አዋቂ የተፈፀመ ጥቃት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ገምተዋል፡፡ ቅዳሜ ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል መዋቅር ላይ የተከሰተውን ግድፈት ተጠቅመው ገንዘብ የወሰዱ አካላትን ለማደን ግብረ ኀይል መቋቋሙ ተገልጿል፡፡ ግብረ ሀይሉ ከብሔራዊ ባንክና ከንግድ ባንክ ባለሙያዎች እንዲሁም ከፀጥታ አካላት የተካተቱበት ነው የተባለ ሲሆን ዓላማው ደግሞ በስድስት ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ከባንኩ ያለ አግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ማስመለስ እና ማጣራት ነው፡፡ ይሁንና ባንኩ በተባለው ሰዓታት ውስጥ የተወሰደበትን የገንዘብ…