14
Nov
ኢትዮጵያ ከባንኮች የውጭ ንግድ ግብይት ብቻ በየወሩ 500 ሚሊዮን ዶላር እያገኘች እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ሐምሌ ወር ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲመራ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከወጪ ንግድ ብቻ በወር በአማካይ 500 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡ ዋና ገዢው አክለውም የባንክ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፊት ከነበረበት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወደ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ማደጉንም ገልጸዋል፡፡ አቶ ማሞ አክለውም ከኹለት ሳምንት በፊት በባንኮች መካከል በተጀመረው የእርስ በርስ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግብይት እንደተካሄደም ተናግረዋል። የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት…