LC

ብሔራዊ ባንክ አስመጪዎች እና ላኪዎች ያለ ባንክ ቅድመ እውቅና እቃ እንዲያዙ ፈቀደ

ብሔራዊ ባንክ አስመጪዎች እና ላኪዎች ያለ ባንክ ቅድመ እውቅና እቃ እንዲያዙ ፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓት እያደረገ ያለውን ሽግግር ለማጠናከር፣ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን የሚያቀሉ አዳዲስ መመሪያዎችን ይፋ አድርጓል።ባንኩ ባወጣው መግለጫ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን ይበልጥ ለማቅለልና በንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት የሆኑ የቢሮክራሲ ሰንሰለቶችን የሚያሳጥሩ ናቸው።በአዲሱ መመሪያ መሰረት የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ እና የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ሂሳብ  ላላቸው ደንበኞች የብድር ደብዳቤ እና የሰነድ መክፈያ ፈቃዶችን ያለ ብሔራዊ ባንክ ቅድመ ሁኔታ ማጽደቅ እንዲችሉ ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።ይህ ማሻሻያ በተለይ በገቢና ወጪ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የጊዜና የቢሮክራሲ ጫናን ያቀላል ተብሎ ይጠበቃል።በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ያላቸው ተቋማት የባንኮችን ቅድመ ፈቃድ ሳይጠብቁ በሰነድ መክፈያ ስምምነት መሠረት የሸቀጦችን የጭነት ትዕዛዝ መስጠት…
Read More