02
Oct
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት እና ተደራሽነት ለማስፋት ከባንክ ጋር ከተያያዙ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች በተጨማሪ ከባንክ ጋር ዝምድና የሌላቸው የግል የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ መመሪያ አውጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት አምስት የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች መስፈርት በማሟላታቸው የስራ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ባንኩ ገልጿል፡፡ ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች መካከል ዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት፣ ኢትዮ ኢንዲፔንደንት፣ ግሎባል፣ ሮቡስት እና ዮጋ ፎርኤክስ የተባሉ የግል የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ቢሮዎቹ ሙሉ ተቀባይነት ያላቸው እና የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛት እና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪ እና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሬ…