01
Jul
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ መወሰኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022) እንዲነሳ ያሳለፈው ወሳኔ ተጠቃሽ ነው። "አሁን ላይ የመንግሥት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉ፣ እንዲሁም መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለሟሟላት የውጭና ገበያ መር የሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየውን ይህ አስገዳጅ መመሪያ አሁን ላይ ማንሣቱ ተገቢ መሆኑን ኮሚቴው አምኖበታል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል። ኮሚቴው ያመነበት ይህ የገንዘብ…