16
Aug
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ስራ መጀመሩን አስታወውቋል። ኩባንያው ባለፉት ሦስት ወራት አስፈላጊ የሲስተም ፍተሻዎችን እና የቴክኒክ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጿል። ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪም ከባንኮች ጋር አብሮ ለመስራት የአጋርነት ስምምነቶች ከመፈራረም ጀምሮ ወኪሎችን መመልመሉን እና ማሰልጠኑንም አስታውቋል። አገልግሎቱን ለማግኘትም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች የሆኑ ሁሉ የኤምፔሳ አገልግሎትን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል። ደንበኞች የአንድሮይድ (Android) እና የአይኦኤስ (IOS) ስልክ ተጠቃሚዎች በሳፋሪኮም መስመራቸው *733# ላይ በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል። የኤምፔሳ መተግበሪያ በ5 ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከፕሌይስቶር በማውረድ መጠቀም የሚችሉት ሲሆን፤ የአይኦኤስ (IOS) ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአፕስቶር…