22
Jan
400 ያህል የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ የጥሪ ማዕከል ሠራተኞች "አይሶን ኤክስፔሪያንስ" የተሰኘ ወኪል ድርጅት ይፈጸምብናል ባሉት የአስተዳደር በደል ሳቢያ ላለፉት 2 ቀናት የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ዋዜማ ዘግቧል። ሠራተኞቹ በዋናነት የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉት፤ በወኪል ድርጅቱ በኩል የሚከፈላቸው ደመወዝ ዝቅተኛ በመሆኑ እንደሆነ ታውቋል። ወኪል ድርጅቱ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሠራተኞችን በተጠና መልኩ ከሥራ እንዲሰናበቱ እያደረገ እንደሆነና ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ብቻ 80 ያህል ሠራተኞችን ሕጋዊነቱን ባልተከተለ መንገድ እንዳሰናበተ ተነግሯል ። ተመሳሳይ የሥራ ዓይነት ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ቋንቋንና ማንነትን መሠረት ያደረገ ሕገወጥ የደመወዝ ልዩነትና አድሎ እንዳለና ድርጅቱ ችግሩን እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ተጠይቆ ሊያስተካክል እንዳልቻለ የድርጅቱ ሰራተኛ ማኅበር አስታውቋል ። የድርጅቱ እህት ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም…