15
Mar
ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ እና ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በሙዚቃዉ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። ከ100 በላይ አንጋፋና ወጣት ድምፃዉያንን እና ሙዚቀኞችን ያስፈረመው ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሙዚቃ አልበሞች እና በሁነቶች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል። ከሰዋሰዉ ድምፃዉያን መካከል አንዱ የሆነዉ እና ከፋሲካ ፆም በኋላ የሚለቀቀዉን የአማኑኤል ሙሴ አልበም ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የስፖንሰርሺፕ ድርሻዉን ወስዷል። በዝናር ዜማ የድምፃዉያን ስብስብ እራሱን ከህዝብ ጋር ያስተዋወቀዉ አማኑኤል ሙሴ ‘’ጥቁር ዉሃ’’ የተሰኘዉ አልበሙም በሳፋሪኮም አጋርነት በሰዋሰዉ አፕ እንደሚለቀቅ ተገልጿል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከአማኑኤል ሙሴ በተጨማሪ ተስፋ የሚጣልባት ወጣት ሴት ድምፃዊ አልበምን ስፖንስር እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን የድምፃዊቷን ማንነት ግን በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙዚቃ አልበምን ስፖንሰር ሲያደርግ የአሁኑ…