Safaricom

የሳፋሪኮሙ ኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ስራ ጀመረ

የሳፋሪኮሙ ኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ስራ ጀመረ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ስራ መጀመሩን አስታወውቋል። ኩባንያው ባለፉት ሦስት ወራት አስፈላጊ የሲስተም ፍተሻዎችን እና የቴክኒክ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጿል። ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪም ከባንኮች ጋር አብሮ ለመስራት የአጋርነት ስምምነቶች ከመፈራረም ጀምሮ ወኪሎችን መመልመሉን እና ማሰልጠኑንም አስታውቋል። አገልግሎቱን ለማግኘትም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች የሆኑ ሁሉ የኤምፔሳ አገልግሎትን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል። ደንበኞች የአንድሮይድ (Android) እና የአይኦኤስ (IOS) ስልክ ተጠቃሚዎች በሳፋሪኮም መስመራቸው *733# ላይ በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል። የኤምፔሳ መተግበሪያ በ5 ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከፕሌይስቶር በማውረድ መጠቀም የሚችሉት ሲሆን፤ የአይኦኤስ (IOS) ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአፕስቶር…
Read More
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአንዋር ሶሳ ምትክ አዲስ ሀላፊ ሾመ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአንዋር ሶሳ ምትክ አዲስ ሀላፊ ሾመ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ሀላፊ ተሾመለት። ላለፉት ሁለት ዓመታት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በሀላፊነት ሲመሩ የቆዩት አንዋር ሶሳ መልቀቃቸው ይታወሳል። ድርጅቱ ባሳለፍነው ሳምንት እንዳለው አንዋር ሶሳ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ በሀላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ አስታውቋል። ይህን ተከትሎም የቀድሞው የኤምቲኤን ኡጋንዳ ሀላፊ የነበሩት ዊም ቫንሄልፑት አንዋር ሶሳን ተክተው ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ሮይተርስ ዘግቧል። በዜግነት ቤልጂየማዊ የሆኑት አዲስ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ ከቀጣዩ መስከረም ጀምሮ ድርጅቱን መምራት ይጀምራሉ። ሳፋሪሎም ኢትዮጵያ በኤምፔሳ አማካኝነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል። በፈረንሳይ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የሆኑት ሔኖክ ተፈራን የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አድርጎ የሾመው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ማፍራቱንም አስታውቋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌሎም ብርቱ…
Read More
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ከሓላፊነት ለቀቁ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ከሓላፊነት ለቀቁ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ከሓላፊነት ለቀቁ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ዓለም አቀፍ ጨረታ ማሸነፉን ተከትሎ ነበር አንዋር ሶሳ ወደ አዲስ አበባ የመጡት። ከ2019 ጀምሮ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አንዋር ሶሳ አሁን ላይ ከሀላፊነት መነሳታቸውን ድርጅታቸው አስታውቋል። ይሁንና ሳፋሪኮም ለምን አንዋር ሶሳን ከሀላፊነት እንዳነሳቸው እስካሁን ይፋ አላደረገም። ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአጭር ወራት ውስጥ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እንዳፈራ አስታውቋል። የኔትወርክ አገልግሎቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም በመከራየት ደንበኞችን እያገለገለ የሚገኘው ሳፋሪ ኮም የኢትዮጵያ ገበያው ያሰበውን ያህል እንዳልሆነለት ከዚህ በፊት መግለጹ አይዘነጋም። ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን መሾሙ ይታወሳል። ላለፉት ሶስት…
Read More
ብሔራዊ ባንክ ለኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቀድ ሰጠ

ብሔራዊ ባንክ ለኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቀድ ሰጠ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል። ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ባንኩ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድን ለሳፋሪ ኮም መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡ ይህም ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ አገር ኩባንያ እንደሚያደርገው የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን አዲስ ሀላፊነት መስጠቱ ይታወሳል። አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች…
Read More
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን ሾመ

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን ሾመ

ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ቴሌኮም ኩባንያ አዲስ ሀላፊ ሾሟል። ላለፉት ሶስት ዓመታት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል። አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች እና ቁጥጥር ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለኢትዮ ነጋሪ እንዳረጋገጠው አምባሳደር ሔኖክ የቀድሞውን የድርጅቱ መሪ የነበሩት ማቲው ሀሪሰንን ተክተዋል። አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ከ2018 እስከ 2022 ድረስ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ20 በላይ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በቅርቡም በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ እንደሚያገኝ ተገልጿል።
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር ሱፐር አፕ የተሰኘ አገልግሎት መስጫውን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር ሱፐር አፕ የተሰኘ አገልግሎት መስጫውን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ በፊት የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጥበት የነበረውን "ቴሌ ብር" መተግበሪያ አዘምኗል። ዛሬ ይፋ ያደረገው ይህ የደንበኞች አገልግሎት ከዚህ በፊት በአገልግሎት ላይ ከነበሩት ሶስት ተጨማሪ አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል። አዲሶቹ አገልግሎቶች የታቀደ ክፍያ፣ ለቡድን ገንዘብ መላክ እና የእድል ጨዋታዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ናቸው። የታቀደ ክፍያ አገልግሎት ደንበኞች የገንዘብ እና አየር ሰዓት ለመላክ እንዲሁም ወርሀዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀኑ ለመክፈል ቀድመው ማቀድ የሚያስችል እንደሆነ ተቋሙ አስታውቋል። ሁለተኛው እና ዛሬ ይፋ የተደረገው የቴሌ ብር ተጨማሪ አገልግሎት ከአንድ በላይ ለሆኑ ተቀባዮች አስቀድመው በሚሞሉት መስፈርት መሰረት በአንዴ መላክ ያስችላልም ተብሏል። ሶስተኛው አዲስ አገልግሎት ደግሞ የእድል ጨዋታ የሚባል ሲሆን አጠቃቀምን መሰረት ያደረገ የአጓጊ ሽልማቶች ባለቤት የሚያደርግ እንደሆነ በፕሮግራሙ…
Read More
ሳፋሪ ኮም ከብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ፈቃድ እንደሚሰጠው ገለጸ

ሳፋሪ ኮም ከብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ፈቃድ እንደሚሰጠው ገለጸ

ብሔራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በቅርቡ ፈቃድ እንደሚሰጥ አስታውቋል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ላገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችለውን ፈቃድ በቅርቡ እንደሚሰጥ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ መጋቢት እንዳሉት መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመንና ለማጠናከር  የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። ከባንክ ውጭ የሆኑ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎችን፣ ፊንቴክና የክፍያ ኤጀንቶችን የመሳሰሉ ተቋማት በክፍያ አገልግሎት ዘርፉ እንዲሳተፉ መደረጉንም ጠቅሰዋል። ባንክ ገዢው አቶ ማሞ አክለውም በአገሪቱ የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢነት ፈቃድ አግኝቶ ሥራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችለውን ፍቃድ በቅርቡ እንደሚያገኝ ተናግረዋል። ይህም ዋና መቀጨውን በኬንያ ያደረገው ሳፋሪኮም በስፋት የሚታወቅበትን የኤም-ፔሳ የሞባይል…
Read More