Newceo

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአንዋር ሶሳ ምትክ አዲስ ሀላፊ ሾመ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአንዋር ሶሳ ምትክ አዲስ ሀላፊ ሾመ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ሀላፊ ተሾመለት። ላለፉት ሁለት ዓመታት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በሀላፊነት ሲመሩ የቆዩት አንዋር ሶሳ መልቀቃቸው ይታወሳል። ድርጅቱ ባሳለፍነው ሳምንት እንዳለው አንዋር ሶሳ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ በሀላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ አስታውቋል። ይህን ተከትሎም የቀድሞው የኤምቲኤን ኡጋንዳ ሀላፊ የነበሩት ዊም ቫንሄልፑት አንዋር ሶሳን ተክተው ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ሮይተርስ ዘግቧል። በዜግነት ቤልጂየማዊ የሆኑት አዲስ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ ከቀጣዩ መስከረም ጀምሮ ድርጅቱን መምራት ይጀምራሉ። ሳፋሪሎም ኢትዮጵያ በኤምፔሳ አማካኝነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል። በፈረንሳይ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የሆኑት ሔኖክ ተፈራን የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አድርጎ የሾመው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ማፍራቱንም አስታውቋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌሎም ብርቱ…
Read More