01
Oct
የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞው ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አንዷለም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተቀላቅለዋል፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንዳስታወቀው የቀድሞውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴን የውጭ ግንኙነት ሃላፊው ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል። አንዷለም የኩባንያው የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ኾነው የተሾሙት፣ የቀድሞው ሃላፊ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ሻወል ከኩባንያው ለቀው ቦይንግ ኩባንያን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ነው። አንዷለም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ያቋቋሙትን አንድ አዲስ የቴሌኮም ኩባንያ በሃላፊነት በመምራት ላይ ነበሩ:: ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የቴሌኮም አገልግሎት ነሀሴ 2014 ዓ.ም ላይ በድሬዳዋ ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡ ድርጅቱ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለ50 በመቶ ህዝብ እንዲሁም በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ደግሞ 98 በመቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም አገልግሎት…