Telecomservices

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 90 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቀደ

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 90 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቀደ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት እቅድን ይፋ አድርገዋል። ስራ አስፈጻሚዋ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በተያዘው በጀት ዓመት ከአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎቶች 90 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል። ድርጅቱ በ2016 በጀት ዓመት 13 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት የተቋሙን አጠቃላይ ደንበኞች ቁጥር ወደ 92 ሚሊዮን የማድረስ ውጥን መያዙንም ሀላፊዋ አክለዋል። የቴሌብር ደንበኞችን ወደ 44 ነጥብ 1 ሚሊዮን፣ የሞባይል ድምጽ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 75 ሚሊዮን እንዲሁን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ወደ 41 ሚሊዮን ማድረስም የተቋሙ ሌላኛው ግብ ነው ተብሏል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቶች የመጠቀም ምጣኔን ወደ 71 በመቶ ለማድረስ መታቀዱን ወይዘሪት ፍሬህይወት ገልጸዋል። የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ከማስፋፋት…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር ሱፐር አፕ የተሰኘ አገልግሎት መስጫውን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር ሱፐር አፕ የተሰኘ አገልግሎት መስጫውን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ በፊት የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጥበት የነበረውን "ቴሌ ብር" መተግበሪያ አዘምኗል። ዛሬ ይፋ ያደረገው ይህ የደንበኞች አገልግሎት ከዚህ በፊት በአገልግሎት ላይ ከነበሩት ሶስት ተጨማሪ አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል። አዲሶቹ አገልግሎቶች የታቀደ ክፍያ፣ ለቡድን ገንዘብ መላክ እና የእድል ጨዋታዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ናቸው። የታቀደ ክፍያ አገልግሎት ደንበኞች የገንዘብ እና አየር ሰዓት ለመላክ እንዲሁም ወርሀዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀኑ ለመክፈል ቀድመው ማቀድ የሚያስችል እንደሆነ ተቋሙ አስታውቋል። ሁለተኛው እና ዛሬ ይፋ የተደረገው የቴሌ ብር ተጨማሪ አገልግሎት ከአንድ በላይ ለሆኑ ተቀባዮች አስቀድመው በሚሞሉት መስፈርት መሰረት በአንዴ መላክ ያስችላልም ተብሏል። ሶስተኛው አዲስ አገልግሎት ደግሞ የእድል ጨዋታ የሚባል ሲሆን አጠቃቀምን መሰረት ያደረገ የአጓጊ ሽልማቶች ባለቤት የሚያደርግ እንደሆነ በፕሮግራሙ…
Read More
ሳፋሪ ኮም ከብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ፈቃድ እንደሚሰጠው ገለጸ

ሳፋሪ ኮም ከብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ፈቃድ እንደሚሰጠው ገለጸ

ብሔራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በቅርቡ ፈቃድ እንደሚሰጥ አስታውቋል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ላገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችለውን ፈቃድ በቅርቡ እንደሚሰጥ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ መጋቢት እንዳሉት መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመንና ለማጠናከር  የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። ከባንክ ውጭ የሆኑ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎችን፣ ፊንቴክና የክፍያ ኤጀንቶችን የመሳሰሉ ተቋማት በክፍያ አገልግሎት ዘርፉ እንዲሳተፉ መደረጉንም ጠቅሰዋል። ባንክ ገዢው አቶ ማሞ አክለውም በአገሪቱ የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢነት ፈቃድ አግኝቶ ሥራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችለውን ፍቃድ በቅርቡ እንደሚያገኝ ተናግረዋል። ይህም ዋና መቀጨውን በኬንያ ያደረገው ሳፋሪኮም በስፋት የሚታወቅበትን የኤም-ፔሳ የሞባይል…
Read More