23
Jun
ድርጅቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 103 ሚሊዮን ዶላር ማስገባቱንም አስታውቋል ኢትዮ ቴሌኮም የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ልሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሪፖርታቸው ላይ እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 52 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡ እንዲሁም ድርጅቱ በሰጣቸው አገልግሎቶች 103 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገባቱንም ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡ የመንግሥትና የንግድ ተቋማት የክፍያ ስርዓታቸውን በቴሌ ብር እንዲፈፅሙ በማድረግ 30.5 ሚሊየን በላይ የቴሌ ብር ተጠቃሚዎችን ማፍራት መቻሉም ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ በቴሌብር አማካኝነት ከ394 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡ በኢንተርኔት ላይ የተጣለው ገደብ ተቋሙን የሚመለከት ሳይሆን፤ በመንግሥት አካል የተጣለ ገደብ ስለሆነ ከሚመለከተው አካል በሚሰጥ ፍቃድ የሚነሳ…