13
Dec
ኤምፔሳ ሳፋሪኮም አዲስ ተጠቃሚ እና ግብይታቸውን በM-PESA የሚያካሒዱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን፣ ወኪሎችን እና ነጋዴዎችን የሚሸልምበት ከታህሳስ 1 ቀን እስከ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የ9ዐ ቀናት የሽልማት መርኃ ግብር ትናንት ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በይፋ አስጀምሯል። ተረክ በኤምፔሳ ደንበኞች እና ድርጅቶች የኤምፔሳ አዲስ ተጠቃሚ በመሆናቸው እና ግብይታቸውን በኤምፔሳ በማካሔዳቸው የእጣ ቁጥሮችን በመሸለም ስለ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቱ የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር እና አጠቃቀሙን ለማጎልበት ያለመ መርኃ ግብር ነው። በእጣዎቹ የሚገኙ ሽልማቶች አራት መኪኖች፣ 12 ባጃጆች፣ 2160 የስልክ ቀፎዎች እና የአየር ሰዓት ስጦታዎች ይሆናሉ፡፡ እያንዳንዳቸው ደንበኞች በአንድ ቀን የሚደርሳቸው ከፍተኛ የእጣ ብዛት 10 ሲሆን ይህም በየእለቱ፣ በሁለት…