WorldBank

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም እና ችግር ላይ የሚገኘውን የፋይናንስ ሁኔታዋን ለመቅረፍ ያግዛት ዘንድ ከአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። በሀገሪቱ የሚታየውን አመታዊ የበጀት ጉድለቷን ለሞሙላት ያግዛት ዘንድ በልዩ ሁኔታ ከአይኤም ኤፍ ብድር መጠየቋን ዘገባው አመላክቷል። የመንግሥት ባለስለጣናት  ባለፈው ሳምንት ከአለም አቀፍ ቦንድ ገዢዎች ጋር በነበራቸው ስብሰባ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2024 መጀመሪያ ሶስት ወራት ከአይ ኤም ኤፍ ጋር የብድር ስምምነት ላይ እደርሳለን ብለው እንድደሚያምኑ ተናግረዋል። ሀገሪቱ ያለት የገቢ ንግድ ማስኬጃ የውጭ ምንዛሬ መጠን ክምችት ዜሮ ነጥብ ሁለት በመቶ ብቻ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ የገጠማትን የበጀት ጉድለት ለመሙላት…
Read More
የዓለም ባንክ ለኢትዮ-ጅቡቲ መንገድ 730 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ

የዓለም ባንክ ለኢትዮ-ጅቡቲ መንገድ 730 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ

የገንዘብ ሚኒስቴርና የዓለም ባንክ ለአፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ፕሮጀክት (በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር ፕሮጀክት) የ730 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት መፈራረማቸው ይፋ ተደርጓል። ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን 90 በመቶ የባህር ንግድን የሚይዘው ስትራቴጂካዊው ከአዲስ አበባ-ጅቡቲ ኮሪደር ጋር በተሳሰረ መልኩ የኢትዮጵያን የሎጅስቲክስና የትስስር አቅም እንደሚያጎለብት ተጠቁሟል። በስምምነቱ መሰረት ለሜኦሶ-ድሬዳዋ መንገድ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን፤ ግንባታው የትራንስፖርት አቅምና ብቃት የሚጨምር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። መንገዱ በሚገነባባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች የጤና፣ ውሃና ትምህርት አገልግሎት ተደራሽነት ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች ድጋፍ እንደሚደረግም ተመላክቷል። ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሺዬቲቭ አካልና የቀጣናዊ ትብብር ማዕቀፍ እንደሆነ ያመለከተው ሚኒስቴሩ፤ ማዕቀፉ አካባቢውን በመሰረተ ልማት የማስተሳሰር ፋይዳም እንዳለው ተጠቅሷል። ስምምነቱን የተፈራረሙትም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ…
Read More
ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያና የአለም ባንክ ለሰው ሀብት ልማት አገልግሎት የሚውል የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በበይነ መረብ በተካሄደ ሥነ-ስርዓት ተፈራርመዋል፡፡ በስምምነቱ ከተፈረመው 400 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 350 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡ የፋይናንስ ድጋፉ ለሰው ሀብት ልማት ማለትም የትምህርትን ጥራትንና ውጤታማነትን ለማሻሻልና የስርዓተ ምግብን አገልግሎት ለማጎልበት የሚውል ሲሆን፤ ከአገልግሎቱም በመላ አገሪቱ የሚገኙ ልጃገረዶችና ታዳጊ ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የሰው ሀብት ልማት አገልግሎቱ በግጭትና ድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የሚያካትት ሲሆን፤ የማህበራዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን ለማጠናከርና ተጠያቂነትን ለማስፈንም አስተዋጽዖ እንዳለው ተነግሯል፡፡ የፋይናንስ ድጋፉ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋጋጥ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በተመረጡ ወረዳዎች የስርዓተ ምግብ አገልግሎትን…
Read More
ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

የኢትዮጵያ መንግስት ለሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር ጠይቋል፡፡ ብድሩ እና እርዳታው የተጠየቀው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ፣ ዓለም ባንክና ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ዕዳ መልሶ ከማሸጋሸግ ለማግኘት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለሪፖርተር እንዳሉት ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከአሜሪካ፣ ፈረንሣይና ሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት መልካም መሆኑ ብድሩ ሊገኝ ይችላል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲስተካከል ጠይቃለች ያሉት አማካሪው ብድሩ ድርድር ከተደረገበት በኋላ ይለቀቃል የሚል ተስፋ መኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ እ.ኤ.አ. በጁላይ ወር መጨረሻ ላይ ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ ይህም ገንዘቡን ለማግኘት ጥሩ እርምጃ ይሆናልም ተብሏል፡፡ 12 ቢሊዮን…
Read More
የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ። ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥ ባንኮች የተበደረችውን ሳይጨምር ከውጭ አበዳሪ ምንጮች ተበድራ ያልመለሰችው የዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል። እንደ ሚኒስቴሩ ሪፖርት ከሆነ ኢትዮጵያ ካለባት 28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ 54 በመቶ የተገኘው ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡ 46 በመቶው ደግሞ ከቻይና እና ከሌሎች ውጭ የግል አበዳሪ ተቋማት የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ባለባት ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ብድር ምክንያትም በዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ምደባ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸው አገሮች ዝርዝር ውስጥ ተመድባለች። በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት የቡድን 20 አገሮች የዕዳ ጫናን ለማቅለል ባዘጋጁት የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሥርዓት ለመጠቀም…
Read More
ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ ማረጋገጫ አገኘች

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ ማረጋገጫ አገኘች

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ እን አይኤምኤፍ ጋር ስታደርገው የነበረው ውይይት ተጠናቋል። የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘባ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ሃላፊዎች ጋር በዋሽንግተን ለአንድ ሳምንት ሲያደርግ የነበረውን ውይይት አጠናቅቋል፡፡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሽ በቀለ በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተመራው ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዳይሬክተሮች ጋር ሲያደርግ የነበረው ውይይት ተጠናቋል፡፡ የፋይናንስ ልዑኩ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ እና ልዑካቸው ጋር ምክክር ማድረጋቸውን እና ለአንድ ሳምንት የቆየውን ውይይት መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡ የተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የልማትና ሰብዓዊ  ድጋፍ ለማግኘት…
Read More