19
Jan
የአፍሪካ ልማት ባንክ ከሁለት ወር በፊት በአዲስ አበባ ያሉ ሁለት የባንኩ ሰራተኞች በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ድብደባ፣ እስር እና እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውቆ ነበር። ባንኩ እንዳለው ሁለት ሰራተኞቹ የቬና የዲልሎማሲ ጥበቃ ስምምነትን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሮ አስተናጋጅ ሀገራት ስምምነትን የጣሰ ክስተት በኢትዮጵያ መፈጸሙንም ገልጿል። የተፈጠረውን ክስተት ለኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ማመልከቱን የሚገልጸው የአፍሪካ ልማት ባንክ ጉዳዩ መፈጸም እንደሌለበት፣ ህግ መጣሱን እና ጉዳዩ ተመርምሮ እርምጃ እንደሚወሰድ በኢትዮጵያ በኩል ቃል ተገብቶልኛል ሲልም በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡ ባንኩ አሁን ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል በገባው መሰረት በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዳልወሰደ እና ጉዳዩ ስለመመርመሩ መረጃ እንዳልሰጠው ገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎም ባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮውን ሊዘጋ እና…