Debt

የኢትዮጵያ ውጭ እዳ መጠን ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ

የኢትዮጵያ ውጭ እዳ መጠን ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ

የአገሪቱ የውጭ ዕዳ መጠን በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 28.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የገንዘብ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው የሩብ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት የዕዳ ሰነድ አመላክቷል። ለዚህ እንደምክንያት የተጠቀሰዉ ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተግባራዊ መደረጉና በተጠቀሱት ሦስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት (IMF) እና ዓለም ባንክ በድምሩ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ብድር የተለቀቀለት በመሆኑ ነዉ ተብሏል። የዕዳ ሰነዱ እንደሚያሳየዉ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከመደረጉ አንድ ወር በፊት ማለትም በሰኔ 2016 ዓ.ም. የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በገንዘብ ሲሰላ 207 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2017 ዓ.ም. መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ወርዷል። የአገሪቱ ጂዲፒ…
Read More
ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ 10 ቢሊዮን ዶላር ብድር መክፈሏ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ 10 ቢሊዮን ዶላር ብድር መክፈሏ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በመሻሻል ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) የመንግስታቸውን የስድስት ወራት አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጊዜ እንዳሌት “ህገ መንግስት ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሟል፤ ስራውን እየሰራ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአማራ ህዝብ በስራ ላይ ባለው ሕገ መንግስት ምክንያት ተንቀሳቅሶ መስራት፣ ሀብት ማፍራት ሌሎች የማንነት ጥያቄዎች እንዳይፈቱ አድርጓል የሚል ጥያቄ አላቸው፡፡ በዚህም መሰረት የአማራ ህዝብ ይህ በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሲዘጋጅ እና ሲጸድቅ በቂ ውይይት እንዳልተደረገበት እንዲሁም የአማራ ህዝብን አግላይ ነው በሚል ጥያቄዎችን ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡ ለአብነትም የአማራ ክልል ወሰን አከላለል ትክክል…
Read More
ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

የኢትዮጵያ መንግስት ለሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር ጠይቋል፡፡ ብድሩ እና እርዳታው የተጠየቀው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ፣ ዓለም ባንክና ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ዕዳ መልሶ ከማሸጋሸግ ለማግኘት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለሪፖርተር እንዳሉት ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከአሜሪካ፣ ፈረንሣይና ሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት መልካም መሆኑ ብድሩ ሊገኝ ይችላል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲስተካከል ጠይቃለች ያሉት አማካሪው ብድሩ ድርድር ከተደረገበት በኋላ ይለቀቃል የሚል ተስፋ መኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ እ.ኤ.አ. በጁላይ ወር መጨረሻ ላይ ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ ይህም ገንዘቡን ለማግኘት ጥሩ እርምጃ ይሆናልም ተብሏል፡፡ 12 ቢሊዮን…
Read More
የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ። ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥ ባንኮች የተበደረችውን ሳይጨምር ከውጭ አበዳሪ ምንጮች ተበድራ ያልመለሰችው የዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል። እንደ ሚኒስቴሩ ሪፖርት ከሆነ ኢትዮጵያ ካለባት 28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ 54 በመቶ የተገኘው ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡ 46 በመቶው ደግሞ ከቻይና እና ከሌሎች ውጭ የግል አበዳሪ ተቋማት የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ባለባት ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ብድር ምክንያትም በዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ምደባ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸው አገሮች ዝርዝር ውስጥ ተመድባለች። በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት የቡድን 20 አገሮች የዕዳ ጫናን ለማቅለል ባዘጋጁት የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሥርዓት ለመጠቀም…
Read More