20
Jan
የአገሪቱ የውጭ ዕዳ መጠን በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 28.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የገንዘብ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው የሩብ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት የዕዳ ሰነድ አመላክቷል። ለዚህ እንደምክንያት የተጠቀሰዉ ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተግባራዊ መደረጉና በተጠቀሱት ሦስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት (IMF) እና ዓለም ባንክ በድምሩ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ብድር የተለቀቀለት በመሆኑ ነዉ ተብሏል። የዕዳ ሰነዱ እንደሚያሳየዉ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከመደረጉ አንድ ወር በፊት ማለትም በሰኔ 2016 ዓ.ም. የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በገንዘብ ሲሰላ 207 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2017 ዓ.ም. መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ወርዷል። የአገሪቱ ጂዲፒ…