29
Nov
ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር እንደሚለቅ አስታውቋል፡፡ ተቋሙ እንዳስታወቀው ብድሩን ለመልቀቅ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ከስምምነት ላይ ደርሷል። ድርጅቱ ብድሩን ለማጽደቅ የተስማማው፣ የድርጅቱ የባለሙያዎች ቡድን ከኅዳር 3 እስከ 17 በአዲስ አበባ ተገኝቶ ኹለተኛውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ግምገማ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ የብድር መልቀቅ ስምምነቱን በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጸድቀውና ወደፊት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ግምገማዎች በየስድስት ወሩ እንደሚካሄዱ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቀረፈና በመደበኛውና በትይዩ የውጭ ሀገራት መገበያያ ምንዛሬዎች መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በታች መውረዱን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ መንግሥት ጥብቅ የገንዘብና ፊስካል ፖሊስ እንዲቀጥል አሳስቧል። ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ሐምሌ ወር ጀምሮ በአይኤምኤፍ እና…