Ethiopiaeconomy

የኢትዮጵያ ውጭ እዳ መጠን ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ

የኢትዮጵያ ውጭ እዳ መጠን ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ

የአገሪቱ የውጭ ዕዳ መጠን በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 28.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የገንዘብ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው የሩብ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት የዕዳ ሰነድ አመላክቷል። ለዚህ እንደምክንያት የተጠቀሰዉ ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተግባራዊ መደረጉና በተጠቀሱት ሦስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት (IMF) እና ዓለም ባንክ በድምሩ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ብድር የተለቀቀለት በመሆኑ ነዉ ተብሏል። የዕዳ ሰነዱ እንደሚያሳየዉ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከመደረጉ አንድ ወር በፊት ማለትም በሰኔ 2016 ዓ.ም. የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በገንዘብ ሲሰላ 207 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2017 ዓ.ም. መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ወርዷል። የአገሪቱ ጂዲፒ…
Read More
ኢትዮጵያ ብድራቸዉን መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ተርታ ተመደበች

ኢትዮጵያ ብድራቸዉን መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ተርታ ተመደበች

መንግስት ከወሰደዉ የረጅም ጊዜ ብድር እና ወለድ አከፋፈል ዙሪያ ከአበዳሪዎች ጋር በዚህ ሳምንት ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ ማቀዱ ተገልጿል የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ በ2014 በዩሮ ቦንድ ከተበደረዉ የ1 ቢሊዮን ዩሮ እና ወለዱን 33 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የመክፈል አቅም ስለመኖሩ አበዳሪዎች ከጥርጣሬ ዉስጥ መገባታቸዉን ብሉምበርግ አስነብቧል። በዘገባዉ ኢትዮጵያ ዛምቢያንና ጋናን በመከተል በአፍሪካ የከሰሩ ሀገራት ተርታን ልትቀላቀል ከጫፍ የደረሰች መሆኑን ዘገባዉ ጠቅሷል። በተያዘዉ ሳምንት ሐሙስ መንግስት ከአበዳሪ አካላት ጋር ዉይይት የማድረግ እቅድ ስለመኖሩ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ መንግስት ከአንዳንድ አበዳሪ አካላት ጋር ባሳለፍነዉ ሳምንት የተገደበ ዉይይት አድርጎ አበዳሪዎች ኢትዮጵያ ያለባትን የ33 ሚሊዮን ዶላር የወለድ እዳ የመክፈል አቅም እንደሌላት ተገንዝበዋል ብሏል። ለዚህም ኢትዮጵያ የዉጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ…
Read More