31
Jul
የዓለም ባንክ የዳይሬክቶች ቦርድ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኢትዮጵያ የ16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ የዓለም ባንክ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫው የገንዘብ ድጋፍና ብድሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን አስታውቋል። በዚህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው ባንኩ፤ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የተራዘመ ብድር ነው ብሏል። የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት 1 ቢሊዮን ዶላር የቀጥታ እርዳታ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ማራዘሚያ እንዲሁም 320 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር በሚል…