parisclub

የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ሊሰጠው ያሰበውን ብድር እና እርዳታ የከለከለው፡፡ ጦርነቱ እንዲቆም ያደረገው የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የቆመውን ጨምሮ አዲስ ብድር እንዲሰጣት ለተቋሙ ጥያቄ ያቀረበች ቢሆንም በተደጋጋሚ የተደረጉ ውይይቶች የታሰበውን ያህል ፍሬ ሳያፈሩ ቆይተዋል፡፡ አይኤምኤፍ በድር ለኢትዮጵያ ከመፍቀዱ በፊት 20 አባላት ያሉት ፓሪስ ክለብ በመባል የሚጠራው የበለጸጉ ሀገራት ስብስብ ብድር እንዲሰጥ ይሁንታ እንዲሰጥ ሲጠበቅ ነበር፡፡ የሀገራትን ብድር የመክፈል አቅም በመገምገም ውሳኔ የሚሰጠው ይህ ስብስብ የኢትዮጵያንም አቅም ሲገመግም ቆይቶ ለአይኤምኤፍ ፈቃድ እንደሰጠ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ከፓሪስ ክለብ በተጨማሪም ሌላኛዋ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ብድር የሰጠችው ቻይና ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ተጨማሪ ብድር እንዲሰጣት ይሁንታቸውንን ሰጥተዋልም…
Read More