15
Oct
ኢትዮጵያ የ 1 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ዕዳዋን ለማዋቀር ስታደርግ የነበረዉ ድርድር ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በ2024 ዓ.ም. ዋናው ዕዳ የሚከፈልበት የአንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ዕዳዋን ለማዋቀር ያደረገው ወሳኝ ጥረት ከቦንድ ባለቤቶች ተወካዮች ጋር ሲያደርገው የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ለዚህ ብድር በየዓመቱ 6.625% ወለድ ለመክፈል መስማማቷ ይታወቃል። የገንዘብ ሚኒስትር እንዳስታወቀው በመስከረም 15 እና ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም መካከል የተካሄደው ውይይት በሁለቱ ወገኖች የቀረቡትን የመጨረሻ የዕዳ ማዋቀር ሃሳቦች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ አልተቻለም። ሚኒስቴሩ ድርድሩ በዚህ ጊዜ ሳይሳካ ቢቀርም፣ "ሰፊ መሻሻል" መመዝገቡን ገልጾ፣ ውይይቱ ወደፊት እንደሚቀጥል ተስፋውን አጠናክሯል። ሁለቱም ወገኖች ለአዲሱ ቦንድ እትም ዋናውን ዕዳ በ15%…