02
Dec
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል ብሏል፡፡ የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡ ባንኮች ከአነስተኛ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ብድሮችን እየሰጡ…