13
Jun
ሳፋሪኮም ከገበያ ኩባንያ ጋር በአጋርነት፣ እንዲሁም የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ድጋፍ ታክሎበት “ሳፋሪኮም ታለንት ክላውድ” የተሰኘ ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል። ፕሮግራሙ የመረጃ መረብን በመጠቀም የሥራ ዕድልን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። ፕሮግራሙ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነና ቀጣዩን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሁም የዲጅታሉ ዓለም መሪዎችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ይህ የተለየ አሠራርን ይዞ የመጣው ፕላትፎርም እስከ 2024 እ.ኤ.አ ማብቂያ ድረስ፣ ለ10 ሺሕ ልዩ ልዩ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች አጠቃላይ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የሥራ ጉዟቸውን ማሳደጊያ ዕድሎችን የሚያቀርብ ነው። ይህንን በማድረግ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂውን ኢንዱስትሪ ዕድገት የገታውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እጥረት ለመቅረፍ ፕሮግራሙ ዒላማ ያደርጋል። "የሳፋሪኮም ታለንት ክላውድ “ለመጪው ዲጂታል ዘመን የኢትዮጵያንን…