BankinginEthiopia

ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

ዋና መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ስታንዳርድ ባንክ በአፍሪካ ትልቁን ያልተነካ ገበያ እየፈለገ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሁለት ሳምንት በኃላ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ ማመልከቻዎችን እንደሚቀበል ከቀናት በፊት መግለፁ አይዘነጋም ። ለዉጪ ፋይናንስ ተቋማት በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንኮች ሆነው እንዲመዘገቡ የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ፍቃደኝነቱን በማሳየት "ስታንደርድ ባንክ" ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሰለፍ ችሏል። በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት ዝቅተኛው የተከፈለ ካፒታል ለዉጪ ባንኮች 100 ሚሊዮን ብር እና ከባንክ ላልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት 25 ሚሊዮን ብር ሀብት ሊኖራቸው ይገባል። ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በባንክ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የውጭ ባለሀብቶች አምስት የሚደርሱ የባንክ ፈቃድ ለመስጠት ማቀዷን ባሳለፍነው ግንቦት…
Read More
አማራ ባንክ ፕሬዝዳንቱን ከሀላፊነት አነሳ

አማራ ባንክ ፕሬዝዳንቱን ከሀላፊነት አነሳ

የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኄኖክ ከበደ ከሓላፊነታቸው ተነሱ የአማራ ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ፕሬዝዳንቱ አቶ ሔኖክ ከበደ ባንኩን ለ460 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ዳርገዋል በሚል ከሀላፊነት አንስቷል፡፡ ባንኩ ከዋና ሥራ አስፈጻሚው በተጨማሪም የኮርፖሬት አገልግሎት ዋና መኰንኑን አቶ ክንዴ አበበን፣ የአፈጻጸም ድክመት አሳይተዋል በሚል በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር  መላኩ ፈንታ ፊርማ ከሓላፊነታቸው አንሥቷል። የባንኩ ቦርድ ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ኹለቱም ከፍተኛ ሓላፊዎች፣ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ፣ በየጊዜው በሚሳዩት የሥራ አፈጻጸም ድክመት፣ የባንኩን ስትራቴጂያዊ ግቦች እና ቁልፍ የአፈጻጸም መመዘኛዎችን ማሳካት አልቻሉም ተብሏል፡፡ ባንኩ በ2014/15 ዓ.ም. ከ306 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ለማስመዝገብ ዐቅዶ የነበረ ቢኾንም፣ ብር 460,286,000 ኪሳራ አስመዝግቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በሌላቸው ሥልጣን ባሳለፉት አስተዳደራዊ…
Read More
ዳሸን ባንክ ደንበኞቹ ከየትኛውም ሀገር ሆነው ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ አስጀመረ

ዳሸን ባንክ ደንበኞቹ ከየትኛውም ሀገር ሆነው ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ አስጀመረ

ዳሸን ባንክ እና ማስተር ካርድ በጋራ በመተባበር "ቨርቹዋል የቅድመ ክፍያ ካርድ" የተሰኘ አገልግሎት በይፉ አስተዋውቀዋል፡፡ ካርዱ ከተለደው እና በሥም ከሚታተመው የፕላስቲክ ካርድ የተለየ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ደንበኞች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሆነው ገንዘባቸውን መጠቀምና ማንቀሳቀስ የሚችሉበት አማራጭ ነው ተብሏል። የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንዳሉት "ዳሸን ባንክ ይህን በአይነቱ የተለየ ካርድ ማስተዋወቁ፤ ባንኩ ለደንበኞቹ ቀላል፣ ምቹና አስተማማኝ የፋይናስ አገልግሎቶችን ይበልጥ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል" ብለዋል፡፡ ዳሽን ባንክ ከዚህ ቀደም "የውጪ ምንዛሬ ሂሳብ" ላላቸው ደንበኞቹ ብቻ የሚያገለግል ካርድ በሥራ ላይ ማዋሉን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ አዲስ የተዋወቀው “ቨርቹዋል የቅድመ ክፍያ ካርድ” በአጠቃላይ ለአለም ዓቀፍ ተጓዦች ታስቦና ከፍተኛ የደህንነት መጠበቂያ ተደርጎለት በአማራጭነት…
Read More
ኢትዮጵያ ለአምስት የውጭ አገር ባንኮች ፍቃድ እንደምትሰጥ ገለጸች

ኢትዮጵያ ለአምስት የውጭ አገር ባንኮች ፍቃድ እንደምትሰጥ ገለጸች

አምስት የውጭ አገር ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። አገር በቀል ባንኮች ከወዲሁ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ እና ቀድሞ የነበራቸውን ስትራቴጂ መከለስ እንዳለባቸውም ባንኩ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ተቋማት ዘርፍ ምክትል ገዥ አቶ ሠለሞን ደስታ እንዳሉት የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማትን ከማጠናከር ጎን ለጎንም የውጭ ባንኮችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው። ‹‹ሥራውን አሁን እያጠናቀቅን ነው። አዋጁን የመከለስ ሥራውንም እያጠናቀቅን ነው:: ከለጋሾች አንዳንድ ግብዓቶችን እየጠየቅን ነው። በወራት ዕድሜ ለህዝብ እንደራሴዎች ይቀርባል:: ስለዚህ ስራው እየተፋጠነ ነው” ብለዋል አቶ ሠለሞን። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እስከ አምስት ለሚደርሱ የውጭ ባንኮች ፈቃድ ለመስጠት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሠለሞን…
Read More
በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባብሏል። በኢትዮጵያ በተለይም የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸው በተለያየ መልኩ ሲገለጹ ቆይቷል። የባንክ ደንበኞችም ለአገልግሎት ባመሩባቸው የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ሲጠይቁ እንዳልሰጧቸው በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተሰተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል። የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት "በኢትዮጵያ በግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል እሚባለው መረጃ ሀሰት ነው" ብለዋል። የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል የተባሉት አምስት ባንኮች ናቸው መባሉን ሰምተናል ፣ "ነገር ግን በሶስት ባንኮች ላይ የተወሰነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሞ ነበር፣ ብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በወሰዷቸው ማስተካከያዎች አሁን ላይ ከአንድ…
Read More
ኢትዮጵያ ለአምስት የውጭ ባለሀብቶች የባንክ ፈቃድ ልትሰጥ መሆኑ ገለጸች

ኢትዮጵያ ለአምስት የውጭ ባለሀብቶች የባንክ ፈቃድ ልትሰጥ መሆኑ ገለጸች

። ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በባንክ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የውጭ ባለሀብቶች አምስት የሚደርሱ የባንክ ፈቃድ ለመስጠት ማቀዷ ተገለጸ፡፡ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ የውጭ ባለሀብቶች የባንክ ፈቃድ እንደሚሰጥ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ይህም የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ አገልግሎት ለውጭ ተፎካካሪዎች ክፍት ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡ እስካሁን የባንኩ ዘርፍ ለውጭ አገራት መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ዝግ ሆኖ የቆየ ሲሆን፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ግን ለውጭ አገራት ተፎካካሪዎች ክፍት እንደሚደረግ ነው የተገለጸው፡፡ በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ዘርፉም ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በጋራ የሚሰሩበት አማራጭ ሊኖር እንደሚችል በምክትል ገዥው በኩል ተጠቅሷል፡፡ የውጭ…
Read More
እናት ባንክ “ለእናቴ” የተሰኘ አገር አቀፍ ጽሑፍ ውድድር  ጀመረ

እናት ባንክ “ለእናቴ” የተሰኘ አገር አቀፍ ጽሑፍ ውድድር  ጀመረ

እናት ባንክ “ለእናቴ” የተሰኘ ኹሉንም የማኅበረሰብ ክፍል የሚያሳትፍና የሚያሽልም አገራዊ የጽሑፍ ውድድር መጀመሩን አስታውቋል። የባንኩ ማርኬቲንግ እና ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አክሊል ግርማ እንዳሉት "ውድድሩ እናት ባንክ ከተመሠረተበት ራዕይና ተልዕኮ አንፃር የሚዛመድ ብሎም የባንኩን ማኅበራዊ እሴት ማዕከል የሚያደርግ አገር አቀፍ መርሐ ግብር ነው" ብለዋል። አቶ አክሊል አክለውም ባንኩ ለዘመናት ለአገርም ሆነ ለቤተሰብ ምሰሶ ለሆኑት የኢትዮጵያ እናቶች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ለአንድ ወር የሚቆይ ሽልማት የሚያስገኝ፣ “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር በይፋ ማስጀመሩን ተናግረዋል። ውድድሩ በዋናነት ኹሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርዝር ጽሑፍ ማለትም ግጥም ባልሆነ በወግ መልክ ወይንም በደብዳቤ ቅርፅ የሚገልጽበትና “ለእናት" የሚልበት መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ዳይሬክተሩ ጨምረው አስረድተዋል። "ኹሉም…
Read More
የኬንያው ኬሲቢ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ድርሻ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ

የኬንያው ኬሲቢ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ድርሻ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ

ዋና መቀመጫውን ኬንያ ናይሮቢ ያደረገው ኬሲቢ ግሩፕ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት ወደ ገበያው ለመግባት አማራጮችን እየገመገመ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ ባንክ የሆነው ኬሲቢ ኬንያን ጨምሮ በቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛንያ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ በባንክ ኢንዱስትሪ እየሰራ ይገኛል። ይህ ባንክ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ባንኮች የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት መወሰኑ ተሰምቷል። ይሁንና የኬንያው ባንክ ከየትኛው የኢትዮጵያ ባንክ አክስዮን ለመግዛት እንደወሰነ አልታወቀም። የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክተር የሆኑት ላውረንስ ኪማቲ ከቢዝነስ ዴይሊ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ ባንክ ገበያ ላይ ቅኝተ ማድረጋቸውን ገልጸው፤ ከተለያዩ ባንኮች ሰዎች ጋር መወያየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ከእነርሱ ጋር ሊሠሩ የሚችሉትን መለየታቸውንም በቆይታቸው ተናግረዋል፡፡ እንደ ላውረንስ የባንኮቹ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የተሻለ…
Read More