12
Jun
ዳሸን ባንክ በስራ ፈጠራ ዘርፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት እየተገበረ ያለው ዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር ለሶስተኛ ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ይካሄዳል፡፡ ባንኩ ውድድሩን ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማካሄድ በአማካሪነት ከቀጠረው ዊቬንቸር ሆልዲንግስ ከተሰኘ ሃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት እንዲሁም የሚዲያ አጋር ከሆነው የአፍሪካ ሬኔሳንስ ቴሌቪዥን (አርትስ ቲቪ) ጋር ዛሬ በዋናው መስሪያ ቤት ስምምነት መፈራረሙን ለኢትዮ ነጋሪ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የዘንድሮው ውድድር በባህር ዳር፣ ደሴ፣ መቀሌ፣አዳማ፣ድሬዳዋ፣ወላይታ፣ ሃዋሳ፣ጅማ እና አዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን በነዚህ ከተሞች በባንኩ ቅርንጫፎች የሰልጣኞች ምዝገባ ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 29-2016 ዓ.ም ይከናወናል፡፡ ለተመዘገቡ ሰልጣኞች በስራ ፈጠራ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያስችል ስልጠና በነዚህ ከተሞች ከተሰጠ በኋላ ሰልጣኞቹ የፈጠራ መነሻ ሃሳባቸውን በፅሁፍ በባንኩ…