Abductioninethiopia

በሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ የተጣለ ቦምብ ፈንድቶ የ4 ልጆች ህይወት አለፈ

በሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ የተጣለ ቦምብ ፈንድቶ የ4 ልጆች ህይወት አለፈ

በአማራ ክልል ከደብረማርቆስ ወደ ደንበጫ የሚወስደው መንገድ በተቃውሞ ምክንያት መዘጋቱም ተገልጿል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ በህጻናት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ እንደ ከተማዋ ፖሊስ መግለጫ ከሆነ ቦምቡ ፈንድቶ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ የነበሩ አራት ልጆች ህይወት አልፏል፡፡ ልጆቹ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ከተጠራቀመ ቆሻሻ ውስጥ ቦምቡ መፈንዳቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡ በቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረው ቦምብ ባደረሰው ጉዳትም አራት ልጆችን ከመግደሉ በተጨማሪ ሁለት ተጨማሪ ህፃናትም ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ህይወታቸው ካለፈ ልጆች ውስጥ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል ከደብረማርቆስ ወደ ደንበጫ የሚወስደው መንገድ በተቃውሞ ምክንያት መዘጋቱ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን…
Read More
የጸጋ በላቸው ጠላፊ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የጸጋ በላቸው ጠላፊ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባልደረባ የሆነችውን ጸጋ በላቸው በማገት ወንጀል የተጠረጠረውና ክትትል ሲደረግበት የቆየው ዋና ሳጂን የኋላ መብራት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፤ ግለሰቡ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው ክትትል፤ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በሀገረ ሰላም ወረዳ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጿል። የጸጥታ ኃይሉ ቀደም ሲል ተበዳይዋን ከጠላፊው ማስጣል መቻሉን ያስታወሰው የሰላምና ጸጥታ ቢሮው፤ በወቅቱ ያመለጠው ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን፤ በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ መቆየቱን ተገልጿል። በዚህም ተጠርጣሪው አካባቢ በመቀየር ፍለጋውን አስቸጋሪ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተደረገው አሰሳ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተመላክቷል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው…
Read More
በባለስልጣን ጠባቂ ወታደር የተጠለፈችው የባንክ ሰራተኛ እስካሁን ያለችበት አልታወቀም

በባለስልጣን ጠባቂ ወታደር የተጠለፈችው የባንክ ሰራተኛ እስካሁን ያለችበት አልታወቀም

የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባለሙያ የሆነችው ፀጋ በላቸው በሐዋሳ ከንቲባ ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም መጠለፏ ተገልጿል። የሲዳማ እና ደቡብ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ይህ መፈጸሙ ብዙዎችን ያስደነገጠ ድርጊት ሆኗል። ባለሙያዋ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ተጠልፋ ከተወሰደች ከሳምንት በላይ ሆኗታል። የተጎጂዋ ቤተሰቦች እንዳሉት የግል ተበዳይ በቤተ ክርስቲያን ደንብ መሰረት የጋብቻ ትምህርት ከወደፊት የትዳር አጋሯ ጋር ተምረው በማጠናቀቅ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለመጋባት ቀን ቆርጠው የቤት ዕቃዎችን በማሟላት ላይ ነበሩ። ይሁን እንጂ ጥቃት አድርሷል በሚል በፖሊስ የሚፈለገው ተጠርጣሪ የግል ተበዳይን በተደጋጋሚ ይዝትባት እና ያስፈራራት እንደነበር ቤተሰቦቿ ተናግረዋል። የግል ተበዳይ ቤተሰቦች ፀጋ ያለችበትን ባለማወቃቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ…
Read More