OLF

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንትና ለሊት በመቂ ከተማ መገደላቸው ተገልጿል። "ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው ተገድለው ነው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል" ሲል ፓርቲያቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢነግ በመግለጫው አክሎም አቶ በቴ ኡርጌሳ ከህግ ውጪ በተፈጸመባቸው ግድያ ህይወታቸው ማለፉን ገልጾ ግድያው የኦሮሞን ጥያቄ ለማፈን እና አመራር አልባ ለማድረግ ነው ሲልም ገልጿል፡፡ በኦሮሞ ህዝብ የሚወደዱ ሰዎችን እያሳደዱ መግደል ቀጥሏል ያለው ኦነግ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ተገድሎ እስካሁን ፍትህ አልተጠም ሲልም ፓርቲው አክሏል፡፡ አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል…
Read More
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራር እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪው ጃል መሮ ፊት ለፊት መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር የተካሄደውን ድርድር የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ አሜሪካ፣ ኖርዌይ እና ኬንያ አስተባባሪ እና አሸማጋይ ሚና መውሰዳቸው ይታወሳል። አሁን የተጀመረውን ንግግር ማን እንደሚያደራድር ግልጽ ባይሆንም፣ ኢጋድ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሚና ሳያስቀጥል እንዳልቀረ ተጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪ አዲስ…
Read More
በኦሮሚያ ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ከ50 በላይ ሰዎች ታገቱ

በኦሮሚያ ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ከ50 በላይ ሰዎች ታገቱ

በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የታገቱትን ሰዎች ለማስለቀቅ ለእያንዳንዳቸው አንድ ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለዳ ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ የነበሩ ከ50 በላይ መንገደኞች ታይተዋል ። እገታውን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው የተባለ ሲሆን ለአንድ ሰው አንድ ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የታጋች ቤተሰቦች ታጣቂዎቹ እየደወሉ መጠየቃቸው ተገልጿል። እገታው የተፈጸመበት ስፍራ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ሲሆን የፌደራል ፖሊስም ሆነ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ታጣቂዎቹ በዜጎች ላይ እገታውን ሲፈጽሙ ማስጣል እንዳልቻለ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ። በዚህ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚያደርሱትን ጥቃት በመፍራት የሌሊት ጉዞ ከቆመ አንድ ዓመት እንዳለፈውም ነዋሪዎቹ…
Read More
በሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ የተጣለ ቦምብ ፈንድቶ የ4 ልጆች ህይወት አለፈ

በሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ የተጣለ ቦምብ ፈንድቶ የ4 ልጆች ህይወት አለፈ

በአማራ ክልል ከደብረማርቆስ ወደ ደንበጫ የሚወስደው መንገድ በተቃውሞ ምክንያት መዘጋቱም ተገልጿል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ በህጻናት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ እንደ ከተማዋ ፖሊስ መግለጫ ከሆነ ቦምቡ ፈንድቶ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ የነበሩ አራት ልጆች ህይወት አልፏል፡፡ ልጆቹ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ከተጠራቀመ ቆሻሻ ውስጥ ቦምቡ መፈንዳቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡ በቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረው ቦምብ ባደረሰው ጉዳትም አራት ልጆችን ከመግደሉ በተጨማሪ ሁለት ተጨማሪ ህፃናትም ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ህይወታቸው ካለፈ ልጆች ውስጥ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል ከደብረማርቆስ ወደ ደንበጫ የሚወስደው መንገድ በተቃውሞ ምክንያት መዘጋቱ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን…
Read More
በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው ሱሉልታ ከተማ በርካታ ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች ታገቱ

በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው ሱሉልታ ከተማ በርካታ ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች ታገቱ

በቅርቡ በተዋቀረው የሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኘው የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸው ተገልጿል። ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፤ በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በማለት በሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” በመባል በአሸባሪነት በተፈረጀው ታጣቂ ቡድን የሚፈጸሙ መሰል ድርጊቶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡ በዚህም “ከአንድ ሳምንት በፊት በአንድ ምሽት ብቻ ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ቁጥራቸው ከ20 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል” ሲል አዲስ ማለዳ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ ሰዎቹ በተወሰዱበት ዕለትም ምንም አይነት የመሳሪያ ድምጽ ባለመሰማቱ የጸጥታ አካላት ደርሰው ሊያስጥሏቸው እንዳልዳቻሉ ጠቅሰዋል። ረቡዕ ግንቦት 30 ቀን…
Read More
የፌደራል መንግሥት እና ኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ድርድር አለመሳካቱ ተገለጸ

የፌደራል መንግሥት እና ኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ድርድር አለመሳካቱ ተገለጸ

የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመውና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቋል ብሏል። ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ነው ያለው ሚንስቴሩ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው የውይይት ምዕራፍ ስምምነት ላይ አልተደረሰም ብሏል። ግጭቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል ሁለቱም አካላት የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ እንደተግባቡ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና እስካሁን ሲመራባቸው በነበሩ መሠረታዊ መርሖች መሠረት ግጭቱን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት መንግስት የጸና አቋም እንዳለው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። ይህንን መልካም አጋጣሚና በውይይት ችግሮችን የመፍታት በጎ ጅምር በመጠቀም ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግሥት ፅኑ አቋም እንዳለው አስታውቋል። አሜሪካ በታንዛኒያ ራስ…
Read More
የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች ተገደሉ

የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ። የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ዛሬ ጠዋት በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል። ኃላፊው ወደ ስራ ለመሄድ ከቤታቸው በወጡበት ጊዜ በተተኮሰባቸው ጥይት እንደተገደሉም ነው የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት በማህበራዊ ገጽ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው። አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ከመሾማቸው አስቀድሞ የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊነትን ጨም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ሲያገለግሉ መቆየታቸውም ተገልጿል። የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ…
Read More
በደራ ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታግተዋል ተባለ

በደራ ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታግተዋል ተባለ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋቾች ቤተሰቦችና ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡  ታጣቂዎቹ ነዋሪዎችን ማገትና ማፈናቀል ከጀመሩ ረዥም ጊዜያት ቢቆጠሩም፣ በ2015 ግን ለተወሰኑ ወራት ፋታ አግኝቶ እንደነበር፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እንደ አዲስ እንደተቀሰቀሰና በዚህም ነዋሪዎቹ እየታገቱ፣ እየተፈናቀሉና ቤት እየተቃጠለ ነው ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የነበሩ የደራ ወረዳ ሰባት ቀበሌዎችን ከሁለት ወራት በፊት በተደረገ ዘመቻ ነፃ ማድረግ ተችሎ እንደነበር ያስረዱት ነዋሪዎቹ፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ግን ጥቃት ማገርሸቱን አክለው ገልጸዋል፡፡ ጋዜጣው በስልክ አነጋገርኳቸው ያላቸው አምስት የወረዳው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂ ቡድኑ እየተሰቃዩ መሆናቸውን፣ በርካታ ሰዎች በየቀኑ እየታገቱና እየተፈናቀሉ እንደሆኑ፣ የታገቱ…
Read More