19
Jun
በአማራ ክልል ከደብረማርቆስ ወደ ደንበጫ የሚወስደው መንገድ በተቃውሞ ምክንያት መዘጋቱም ተገልጿል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ በህጻናት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ እንደ ከተማዋ ፖሊስ መግለጫ ከሆነ ቦምቡ ፈንድቶ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ የነበሩ አራት ልጆች ህይወት አልፏል፡፡ ልጆቹ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ከተጠራቀመ ቆሻሻ ውስጥ ቦምቡ መፈንዳቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡ በቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረው ቦምብ ባደረሰው ጉዳትም አራት ልጆችን ከመግደሉ በተጨማሪ ሁለት ተጨማሪ ህፃናትም ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ህይወታቸው ካለፈ ልጆች ውስጥ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል ከደብረማርቆስ ወደ ደንበጫ የሚወስደው መንገድ በተቃውሞ ምክንያት መዘጋቱ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን…