06
Jun
የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባልደረባ የሆነችውን ጸጋ በላቸው በማገት ወንጀል የተጠረጠረውና ክትትል ሲደረግበት የቆየው ዋና ሳጂን የኋላ መብራት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፤ ግለሰቡ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው ክትትል፤ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በሀገረ ሰላም ወረዳ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጿል። የጸጥታ ኃይሉ ቀደም ሲል ተበዳይዋን ከጠላፊው ማስጣል መቻሉን ያስታወሰው የሰላምና ጸጥታ ቢሮው፤ በወቅቱ ያመለጠው ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን፤ በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ መቆየቱን ተገልጿል። በዚህም ተጠርጣሪው አካባቢ በመቀየር ፍለጋውን አስቸጋሪ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተደረገው አሰሳ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተመላክቷል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው…