09
Dec
ዳሸን ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ባስመዘገበው የላቀ አፈጻፀም የ“ዘባንከር” ሽልማት ተሸላሚ ሆነ ባንኮችን በተለያዮ የምርጥ አፈጻጸም መለኪያዎች የሚመዝነው የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚያሳትመው ዘባንከር መጽሔት ዳሸን ባንክ የ2024 የኢትዮጵያ አሸናፊ ሆኗል፡፡ የዳሸን ባንክ ቺፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ወ/ሪት እየሩሳሌም ዋጋው እና የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፋይናንስ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በእንግሊዝ ሎንዶን ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው ዳሸን ባንክ በዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ከተለያዩ አለምአቀፍና አህጉራዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የፈጠረው ውጤታማ ጥምረት ለሽልማት አብቅቶታል ተብሏል፡፡ አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱ ዳሸን ባንክ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነትና እና ከተለያዩ አለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት…