LONDON

ብሪታንያ ከመቅደላ የዘረፈቻቸውን ቅርሶች ለኢትዮጵያ አስረከበች

ብሪታንያ ከመቅደላ የዘረፈቻቸውን ቅርሶች ለኢትዮጵያ አስረከበች

ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቅርሶች በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመለሱ በ1868 በአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት በብሪታንያ ተዘርፈው የተወሰዱ የኢትዮጵያ ቅርሶች መመለሳቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ ከተመለሱት ቅርሶች መካከል በ1868 ዓ.ም ከመቅደላ የተዘረፈ የመድሃኒያለም ታቦት፣ የልኡል አለማየሁ የጸጉር ዘለላ፣ ከብር የተሰሩና በነሃስ የተለበጡ ሦስት ዋንጫዎች እንዲሁም በዘመኑ ጦርነት ላይ የዋለ የጦር ጋሻ እንደሚገኙበት ገልጿል፡፡ ለንደን በሚገኘው የአቴናየም ክለብ በተካሄደው የቅርሶቹ ርክክብ ሥነ ስርዓት ላይ፤ በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልኡካን ቡድን፣ የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ተወካይ፣ የብሪታኒያ ፓርላማ አባላት፣ ቅርሶቹን ለማሰመለስ የተባበሩ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይም አምባሳደር ተፈሪ መለሰ፤ የተመለሱት የተለያዩ…
Read More
የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ለዲያስፓራ ኢትዮጵያውያን ቤት መሸጥ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ለዲያስፓራ ኢትዮጵያውያን ቤት መሸጥ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ

ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ ሀይል እና እቅድ ወደ ስራ መግባቱን የገለጸው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሃገር ውስጥ ካለው ነዋሪ ባሻገር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ኘሮጀክት ለመጀመር ዝግጅት እያደረኩ ነው ብሏል። ስለ ኘሮጀክቱ እና ስለተቋሙ ገለፃ ለማድረግም በኮርፓሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል የተመራ ልዑክ ወደ ብሪታንያ በማምራት በዚያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የማህበረሰብ አመራሮች ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውንን ተጠቃሚ ለማድረግ በአዲስ መልክ ያቀደውን የቤት ልማት ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ተጨማሪ ሀሳበችንና ተሞክሮዎችን መሰብሰቡ ተገልጻል። ከዚሁ ጎን ለጎን በዋና ስራ አስፈፃሚው የሚመራው የልዑካን ቡድኑ በለንደንና አካባቢው በሚገኙ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት…
Read More
ከኢትዮጵያ የተዘረፉ 538 ቅርሶች በእንግሊዝ ተገኙ

ከኢትዮጵያ የተዘረፉ 538 ቅርሶች በእንግሊዝ ተገኙ

ከኢትዮጵያ የተዘረፉ 538 ያህል ቅርሶች በእንግሊዝ ተገኙ ከኢትዮጵያ የተዘረፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ባሕላዊ ቅርሶች በእንግሊዝ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ ቅርሶቹ እንግሊዝ ኢትዮጵያን በፈረንጆቹ 1868 ላይ በወረረችበት ወቅት በወታደሮች መዘረፋቸውም ተጠቁሟል፡፡ “ዘ ፕሪንስ ኤንድ ዘ ፕላንደር” ወደ አማርኛ ሲመለስ “ልዑሉ እና ዘረፋው” የተሠኘ መፅሐፍ የደረሱት እንግሊዛዊው አንድሪው ሄቨንስ 538 ያህል የኢትዮጵያ ቅርሶች እንዴት ወደ እንግሊዝ እንደተወሰዱ በመፅሐፉ በዝርዝር አመላክተዋልም ነው የተባለው፡፡ ደራሲው ቅርሶቹ በለንደን እንደሚገኙ መጠቆማቸውንም ኤቭኒንግ ስታንዳርድ የተሰኘው የሀገሪቷ የዜና ምንጭ ዘግቧል። የጠቀሷቸው ቅርሶች ከጥቃቅን እና ከተቀደሱ መፅሐፍት እና ቅርሶች ጀምሮ የከበሩ መዋቢያ የዕጅ አምባሮች ፣ የነገሥታት አልባሳት ፣ የነገሥታት የጋብቻ አልባሳት ፣ ዘውድ እና ታቦታት ይገኙበታል፡፡ የእንግሊዝ ወታደሮች ቅርሶቹን በያዟቸው ቦርሳዎች እና…
Read More