29
May
ኢትዮጵያ ባለፋት አስር ወራት ከአበባ ኤክስፓርት ከ 3 መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች፡፡ የሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት ዘርፍ በተለይም የአበባ ኤክስፖርት ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦን እያበረከተ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንት እና ምርት ግብይት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ አበበ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፋት አስር ወራት 79 ሺህ 819 ቶን የአበባ ምርት ለውጪ ገበያ በማቅረብ 392 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አግኝታለች ብለዋል። የኢትዮጵያ የአበባ ምርት በአብዛኛው ወደ አውሮፓና ኤዥያ ሀገራት እንደሚላክ የተናገሩት ስራ አስፈፃሚው ምርጥ አስር ተብለው ከተለዩት ተቀባይ ሀገራት መካከል ደግሞ ኔዘርላንድ ትልቁን ድርሻ ትይዛለች ብለዋል። በበጀት አመቱ አስር ወራት ከእቅድ አፈፃፀም አንጻር ሲታይ የተገኘው ገቢ…