18
Jul
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር፡፡ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቋል፡፡ የተገኘው ገቢ ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር የ4.6 በመቶ ወይም በ166 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርናው ዘርፍ 76 በመቶ በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን ማኑፋክቸሪንግ ማእድን ፣ኤሌክትሪክና ሌሎች በተከታታይ የሚገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ከውጭ ሀገራት ግዢ በመፈጸም ለተጠቃሚዎች እንደተሰራጨም ተገልጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን…