09
Oct
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ የንግድ ማስጀመሪያው ፕሮግራሙን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ታድመዋል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ የንግድና ቀጠናዊ ተስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የAfCFTA ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ባለፈ ለንግድ ዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈም ለኢትዮጵያን ንግድ ዘርፍ መስፈንጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡ ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ…