በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
የንግድ ማስጀመሪያው ፕሮግራሙን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ታድመዋል።
ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ተስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የAfCFTA ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ባለፈ ለንግድ ዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈም ለኢትዮጵያን ንግድ ዘርፍ መስፈንጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡
ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ተልከዋል፡፡
ስምምነቱ ከ55 በላይ አገራት እና ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ህዝብን የሚያቅፍ ሲሆን፣ የ3.4 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) ያለው ትልቅ ኢኮኖሚ ይፈጥራል።
ይህ ደግሞ ለአገሪቱ ላኪዎች፣ አምራቾች እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶች ሥራ ፈጣሪዎች ከፍተኛ የገበያ እድል ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ በAfCFTA ማዕቀፍ መሠረት 97 በመቶ የሚሆኑ የታሪፍ ምጣኔዎችን በሂደት ዜሮ ለማድረግ ማሻሻያ ያደረገች ሲሆን፣ ቀሪውን 3 በመቶ ደግሞ ለጥበቃ (Protection) እንደምትጠቀም አስታውቃለች።
ለመጀመሪያ ጊዜ ለግብይት የተላኩት ምርቶች ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ሲሆኑ ምርቶቹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ እና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ተልከዋል።