Trade

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይትን በይፋ ተቀላቀለች

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይትን በይፋ ተቀላቀለች

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ የንግድ ማስጀመሪያው ፕሮግራሙን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ታድመዋል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ የንግድና ቀጠናዊ ተስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የAfCFTA ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ባለፈ ለንግድ ዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈም ለኢትዮጵያን ንግድ ዘርፍ መስፈንጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡ ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ…
Read More
ኢትዮጵያ ከ18 ሀገራት ጋር የንግድ ድርድር ጀመረች

ኢትዮጵያ ከ18 ሀገራት ጋር የንግድ ድርድር ጀመረች

ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት ድርድር ሂደት 6ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ፤ በሁለትዮሽ ንግድ ድርድር ዙሪያ 18 ሀገራት ጋር ድርድር ማድረግ መጀመሯን ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት 6ኛ የሥራ ቡድን ስብሰባ ባለፈው ሳምንት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ መካሄዱ ይታወሳል። ይህ ስብሰባ ኢትዮጵያ የድርጅቱን አባልነት ጥያቄ ባቀረበች ከ20 ዓመታት በላይ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ የተመዘገበበት እንደነበር ሚኒስቴሩ ገልጿል። የድርድሩ ቡድን መሪ፣ ዋና ተደራዳሪ እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የድርድር ሂደቱን አስመልክቶ፤ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን እና ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያለው የንግድ ትስስር እንድታጎለብት ለማድረግ ብርቱ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡ ከዚህ…
Read More