27
Dec
የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ድርድርን እና ቀጣናዊ የንግድ ትስስሮችን የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ በአዲስ መልክ መቋቋሙን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችን እንዲሁም ባለሙያዎችን ያካተተ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በተለያዩ ጊዜያት ፍላጎቷን ብታሳይም ከአባል አገራት ለሚነሱ አንዳንድ የንግድ ዘርፍ አካታችነት አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ባለመቻሏ ድርጅቱን መቀላቀል ሳትችል ቆይታለች። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ከአምስት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን ሲመጣ የዓለም ንግድን በአባልነት መቀላቀል እንደሚፈልግ በይፋ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ መንግስት ከወሰዳቸው ስር ነቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና አዳዲስ ለውጦች መካከል አገሪቱን በ2021 የአለም ንግድ ድርጅት አባል ማድረግ ይገኝበታል። በዚህም ከ2020 አንስቶ ድርድር እንደ አዲስ…