16
Oct
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር እንደገለጸው ባለፉት ሦስት ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበቻቸው ምርቶች 2 ነጥብ 48 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታውቋል። ሚንስቴሩ በበጀት ዓመቱ ሩብ ወራት ጥራጥሬንና የቅባት እህሎችን ከመሳሰሉ ምርቶች 149 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጿል። በተያዘው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ዘርፉ ለማግኘት የታቀደው አጠቃላይ ገቢ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው ገቢ የ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ አለው። ከፍተኛ ገቢ ካስገኙ ምርቶች መካከል ቡና ሲሆን 762 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገልጿል። ገቢው የተገኘው፣ 113 ሺህ 542 ቶን ቡና በመላክ ነው የተባለ ሲሆን ከ151 ሺሕ 969 ቶን በላይ ቡና በመላክ፣ 622 ነጥብ 5…