03
Jan
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግድ ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ በተጠቀሱት ጊዜያት ውስጥ 480 ሺህ ቶን የተለያዩ ምርቶችን ወደ ተለያዩ ሀገራት በመላክ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደተገኘ ተገልጿል፡፡ የተገኘው ገቢ ካምናው ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸር የ947 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አሳይቷል ተብሏል፡፡ ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ ግብርና 53 ነጥብ 25 በመቶ ድርሻ ሲይዝ ማዕድን 37 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ 5 ነጥብ 43 በመቶ እንዲሁም ኤሌክትሪክና ሌሎች 4 ነጥብ 33 በመቶ ድርሻ ይዘዋል፡፡ ወርቅ፣ ቡና፣ ኤሌክትሪክ እና የጥራጥሬ ምርቶች በገቢም ሆነ በመጠን ከዕቅዳችው በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ምርቶች መሆናቸውን የሚስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡ ከተላኩ ምርቶች መካከል 150 ሺህ ቶን…