29
Jun
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀገሪቱ ዋነኛ የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ በሆነው የቡና ምርት ላይ የሚፈጸመውን ህገ-ወጥ ዝውውር (ኮንትሮባንድ) ለመግታት፣ ከተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥብቅ የሆኑ የቁጥጥርና የቅጣት እርምጃዎችን መተግበር መጀመሩን አስታውቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰፊሳ አባቡ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ የቡና ንግድ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በእጅጉ እየጎዳ በመሆኑ፣ ድርጊቱን ለመከላከል አዲስ የክትትል ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል። በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ ህገ-ወጥ የቡና ዝውውርን ለማስቆም ከፌዴራልና ክልል ፖሊስ፣ ከጉምሩክ ባለስልጣን እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም ኋላፊው አክለዋል። በመሆኑም ያለ ህጋዊ ፈቃድና ሰነድ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የቡና ምርት ሙሉ በሙሉ በመንግስት ይወረሳል ተብሏል። በህገ-ወጥ…