importexport

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ወደ ጅቡቲ በባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዝ ጀመረች ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ዉስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ ያገለገል የነበረዉ የአዳማ - ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የቁም እንስሳትን ማጓጓዝ ጀምሯል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ እንደገለፁት በአዳማ በኩል የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርትን ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ከመጨመሩም ባሻገር የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል። ከአዳማ ወደ ጅቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈፃሚው ይህን አገልግሎት በመጀመራችን አቅማችን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል። በባቡር ትራንስፖርት በመጠቀም ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከው የእንስሳት ንግድ የህገወጥ ንግድ እንቅስቀሴንን ከማስቀረቱ ባለፈ ጊዜ…
Read More
የኢትዮጵያ ውጪ ንግድ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ ውጪ ንግድ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር፡፡ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቋል፡፡ የተገኘው ገቢ ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር የ4.6 በመቶ ወይም በ166 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርናው ዘርፍ 76 በመቶ በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን ማኑፋክቸሪንግ ማእድን ፣ኤሌክትሪክና ሌሎች በተከታታይ የሚገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ከውጭ ሀገራት ግዢ በመፈጸም ለተጠቃሚዎች እንደተሰራጨም ተገልጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን…
Read More
ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላከ የቡና ንግድ በታሪክ ከፍተኛ የተባለዉን ገቢ ማግኘቷን አስታውቃለች፡፡ ኢትዮጵያ ከቡና ወጪ ንግድ በዘንድሮው በጀት አመት ከአንድ ነጥብ 4 ቢሊዮን  ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በ2016 በጀት አመት ከቡና ሽያጭ በመጠንም ሆነ በገቢ ከፍተኛ የሆነ ውጤት አስመዝግባለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት 298 ሺህ 500  ቶን ቡና ለውጪ ገበያ አቅርባ 1 ነጥብ 43 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠንም ሆነ በገቢ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ  ጨምረው ገልፀዋል። የተላከው የቡና መጠን በ20 በመቶ እንዲሁም በዋጋ ደረጃም…
Read More
ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ዳንኤል ኃ/ሚካኤል የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተደርገው ተሾመዋል፡፡ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር (ኢዲአር) ቺፍ ቴክኒካል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጂነር ዳንኤል ኃ/ሚካኤል ከሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ ተሾመዋል። የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ለኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት አብዲ ዘነበ ምትክ ዳንኤልን ኃ/ሚካኤልን ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሆኑ መድበዋል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተጓዦችና የጭነት አገልግሎት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ይታወሳል። ማኅበሩ በየቀኑ ከ700 እስከ 1 ሺህ ሰዎችን የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ155…
Read More