24
Sep
ኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ወደ ጅቡቲ በባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዝ ጀመረች ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ዉስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ ያገለገል የነበረዉ የአዳማ - ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የቁም እንስሳትን ማጓጓዝ ጀምሯል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ እንደገለፁት በአዳማ በኩል የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርትን ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ከመጨመሩም ባሻገር የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል። ከአዳማ ወደ ጅቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈፃሚው ይህን አገልግሎት በመጀመራችን አቅማችን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል። በባቡር ትራንስፖርት በመጠቀም ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከው የእንስሳት ንግድ የህገወጥ ንግድ እንቅስቀሴንን ከማስቀረቱ ባለፈ ጊዜ…