Livestock

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ወደ ጅቡቲ በባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዝ ጀመረች ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ዉስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ ያገለገል የነበረዉ የአዳማ - ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የቁም እንስሳትን ማጓጓዝ ጀምሯል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ እንደገለፁት በአዳማ በኩል የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርትን ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ከመጨመሩም ባሻገር የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል። ከአዳማ ወደ ጅቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈፃሚው ይህን አገልግሎት በመጀመራችን አቅማችን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል። በባቡር ትራንስፖርት በመጠቀም ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከው የእንስሳት ንግድ የህገወጥ ንግድ እንቅስቀሴንን ከማስቀረቱ ባለፈ ጊዜ…
Read More
ኢትዮጵያ በሕገ- ወጥ እንስሳት ንግድ ምክንት በየወሩ 17 ሚሊዮን ዶላር እያጣች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በሕገ- ወጥ እንስሳት ንግድ ምክንት በየወሩ 17 ሚሊዮን ዶላር እያጣች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በቀን ከ1 ሺህ 200 በላይ የቁም እንስሳት በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገር በመውጣታቸው በየቀኑ ከ630 ሺህ ዶላር በላይ እንደምታጣ ተገልጿል። በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለአገልግሎት የሚወሉ መድኃኒቶችም የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው በጤና ሥርዓቱ ላይ ጫና እያሳደሩ መሆኑም ተገልጿል። በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ሕገ-ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ ዛሬ ተካሂዷል። ምክር ቤቱ ሕገ-ወጥ ንግድ በስፋት በሚታይባቸው ዘርፎች ላይ ያካሄዳቸውን ጥናቶች ይፋ አድርጓል። ጥናቶቹ በቁም እንስሳት፣ በመድኃኒት፣ በጨርቃጨርቅ፣ በሎጂስቲክስ ሥርዓት ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችና ንግድን በተመለከቱ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተካሄዱ ናቸው። አሁን ላይ የቁም እንስሳትና የመድኃኒት ሕገ-ወጥ ንግድ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ በጥናቱ ተመላክቷል። በኢንዱስትሪ…
Read More