09
Jan
አየር መንገዱ በአፍሪካ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ብዛት ወደ 35 አሳድጓል። ወደ ካዛብላንካ የሚደረገው የጭነት በረራ ከ100 ቶን በላይ የመሸከም አቅም ባለው ቦይንግ 777-200F የእቃ ጭነት አውሮፕላን ነው ተብሏል። የኢትዮጵ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው “ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት መስጠት በመጀመራችን ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል በመልዕክታቸው። ይህ በረራ መጀመሩ በአፍሪካ ያለንን የዕቃ ጭነት መዳረሻ ቁጥር 35 ሲያደርስ፤ በተመሳሳይ ብሔራዊ አየር መንገዱ በእቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት በረራ መዳረሻዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ እና በዓለም የአየር የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስክ ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ…