AFTA

ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር የባቡር ትራንስፖርት የመገንባት እቅድ እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር የባቡር ትራንስፖርት የመገንባት እቅድ እንዳላት ገለጸች

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠናን ታሳቢ ያደረገ የባቡር መስመር ትስስር ወደ ሁሉም የጎረቤት ሀገራት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል። የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን ታሳቢ ያደረገ እና ኢትዮጵያን ከሁሉም የጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያስተሳስር የባቡር መስመር እየተሰራ እንደሚገኝ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል። የባቡር ትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ከፍተኛ በመሆኑ ረዥም ርቀትን፣ መሰረተ ልማትን እንዲሁም ንግድና ቀጠናዊ ትስስርን ታሳቢ አድርጎ እንደሚሰራ የገለፁት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ናቸው። በመሆኑም የባቡር መስመር ዝርጋታ በሀገር ውስጥ የሚቆም ሳይሆን፤ በሁሉም አቅጣጫ ከሚገኙ ጎረቤት ሀገራትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር በጋራ ለመነገድና ለመስራት የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል። ከጎረቤት ሀገራት ባሻገር ደግሞ የአፍሪካን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ከማስፋፋት አንፃር ታሳቢ ያደረገ…
Read More
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና እድል ምርቶቿን ወደ ሶስት ሀገራት እየላከች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና እድል ምርቶቿን ወደ ሶስት ሀገራት እየላከች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነትን መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ መጀመሯ ይታወሳል። ሀገሪቱ ምርቶቿን ወደ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት በመላክ ላይ ነች የተባለ ሲሆን ምርቶቹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በኩል እየተላኩ እንደሆነም ተገልጿል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንዳሉት ከተላኩት የመጀመሪያ የወጪ ንግድ ምርቶች መካከል ስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡና እና ጥራጥሬ እህሎች ይገኙበታል። ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ደግኖ የኢትዮጵያ ምርቶሽ የተላከባቸው ሀገራት እንደሆኑ ተጠቅሷል። ምርቶቹ በአብዛኛው የተጓጓዙት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አማካኝነት ሲሆን፤ አየር መንገዱ ለነፃ ንግድ ቀጠናው ትግበራ ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ነው ብለዋል አቶ ወንድሙ። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነትን…
Read More