19
Aug
ኢትዮጵያ የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መንገደኞችን ከማስተናገድ አንጻር እቅሙ ተዳክሟል በሚል ምክንያት በ12 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ኤርፖርት ለመገንባት ማቀዷ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በ12 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት የዲዛይን ስራው ተጠናቆ የተቋራጭ ድርጅቶች መረጣ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህ ኤርፖርት ግንባታ የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ዓለም አቀፍ ተቋራጮች እንዲወዳደሩ ዓለም አቀፍ የመጀመሪያ ዙሪ ማስታወቂያ መውጣቱን ተከትሎ የአሜሪካ ፣ አውሮፓ ፣ እስያ እና ሌሎችም ሀገራት ፍላጎታቸውን አሳውቀዋል። በዚህም መሰረት የቻይና የግንባታ ተቋማት በብዛት ፍላጎታቸውን እንዳሳዩ ተገልጿል። በቀረበው የእጩዎች ዝርዝር መሰረት ከወጡት አራት ዋና ዋና የሥራ ክፍሎች ውስጥ የቻይና ተቋማት በተናጠልና በቅይጥ በብዛት ተካተዋል። የቻይና ኮሙኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (CCCC)፣ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን…