electricity

ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ እንደምትጀምር ገለጸች

ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ እንደምትጀምር ገለጸች

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሀይል የማመንጨት አቅም በዕጥፍ ጨምሯል ተብሏል ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የምታመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ከእጥፍ በላይ ማሳደጓን አስታወቀች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸዉ ከግድቡ የሚመረተዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል። ከዚሕ ቀደም ሥራ የጀመሩት ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያመነጩ ቆይተዋል፡፡ ሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች ደግሞ እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል እንደሚያመነጩ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የሚያወዛግባትን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ መገንባት የጀመረችዉ ከመጋቢት 2003 ዓ.ም ጀምሮ ነበር። ይህ የአፍሪካ ትልቁ ግድብ በ2014 ዓ.ም ላይ…
Read More
አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት ከአለም አቀፉ አሚአ ፓወር ኩባንያ ጋር ተስማምታለች፡፡ ስምምነቱ በዱባይ ከአራት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ እና አሚአ ኩባንያ ሀላፊዎች መካከል ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ለሚገነባዉ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ለማልማት በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ከተሰማራው እና መቀመጫዉን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ካደረገዉ ከአሚአ ፓወር ጋር ስምምነት አድርጓል። በታዳሽ ኃይል ልማት፣ ግንባታና አስተዳደር ዘርፍ የተሰማራው አሚአ ፓወር በአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል 300 ሜጋ ዋት አመንጭቶ ለኢትዮጵያ ለመሸጭ ነው ሥምምነቱን የፈረመው። በኢትዮጵያ 300 ሜጋ ዋት የንፋስ ሃይል ፕሮጀክትን ለማልማት እና ለማንቀሳቀስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር የኃይል ግዢ ስምምነት እና የትግበራ ስምምነት መፈራረሙን ያስታወቀው…
Read More
ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ በመሸመት ቀዳሚ አገር ሆነች

ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ በመሸመት ቀዳሚ አገር ሆነች

ኬንያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸመት ቀዳሚ መሆኗ የተገለጸ ሲሆን፤ በተለይ ባለፈው ጥር ወር ያስገባቸው የኃይል መጠን በታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡ ይህ የሆነውም በምስራቅ አፍሪካ ባጋጠመው አስከፊ ድርቅ ምክንያት የኃይል ማመንጫ ግድቦች ውሃቸው በመድረቁ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል፡፡ ከኬንያ ስታትስቲክስ ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ አገሪቱ ባለፈው ጥር ወር 68 ነጥብ 48 ሚሊዮን ኪሎዋት ኤሌክትሪክ ኃይል አስገብታለች፡፡ ኹለቱ አገራት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ የኤሌክትሪክ ኃይል በቅናሽ ለመገበያየት ከተስማሙ በኋላ፤ ኬንያ 39 ሚሊዮን ዩኒት ኃይል ከኢትዮጵያ ማስገባቷ ተነግሯል፡፡ በዚህም አገሪቷ በርካሽ ዋጋ ኃይል ለማስገባት ከተስማማች በኋላ ጥር ላይ 200 ሜጋዋት የኤሌክትርክ ኃይል ከኢትዮጵያ ማስገባቷ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም የኃይል አቅርቦቱን ለማረጋጋት እንዳስቻላት ተጠቁሟል፡፡ ኬንያ…
Read More
ሱዳን ለኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ክፍያ አለመፈጸሟ ተገለጸ

ሱዳን ለኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ክፍያ አለመፈጸሟ ተገለጸ

ሱዳን ለኢትዮጵያ መክፈል ያለባትን የኤሌክትሪክ ክፍያ ባለመክፈሏ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ተጠይቋል። ሱዳን ከኢትዮጵያ ለምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ በየወሩ ሙሉ ለሙሉ መክፈል ቢኖርባትም ካለፈው ዓመት ጀምሮ ክፍያዋን በማቆረጧ፣ ተከፍሎ ያላለቀና መጠኑ ያልተገለጸ በርካታ ሒሳብ እንዳለባት ተገልጿል። ኢትዮጵያ ለሦስት የጎረቤት አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል ትልካለች። ሀገሮቹም አንደኛው ወር ሲጠናቀቅ የሚቀጥለው ወር ላይ ሆነው ባለፈው ወር ለተላከው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ክፍያ ይፈጽማሉ። ሱዳንም በእንዲህ ዓይነት አሠራር መክፈል የነበረባትን ቢሆንም ክፍያ አየቆራረጡ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን ጨርሰው እየከፈሉና እያጠናቀቁ አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ተናግረዋል። "የአንድ ወር ሙሉ የሚከፈልበት፣ ሌላው ሙሉውን የማይከፈልበት፣ አልያም ደግሞ በከፊል ከሌሎች ክፍያዎች ጋር እያደረጉ…
Read More